በዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ቤት ለሚማሩ 59 የ5ኛ ዓመት የሕግ ተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም ከዚህ ቀደም በተለያዩ ቦታዎች የሕግ ትምህርታቸውን ተከታትለው የመውጫ ፈተናውን ላላለፉ 87 ተማሪዎች ከሐምሌ 27-30/2013 ዓ/ም የ2013 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የሕግ መውጫ ፈተና ተሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የሕግ ት/ክፍል ኃላፊ አቶ ጎድሴንድ ኮኖፋ የሕግ መውጫ ፈተና ተማሪዎች በሥርዓተ ትምህርቱ ላይ የተቀመጠውን መሠረታዊ ክሂሎትና ዕውቀት ምን ያህል እንደተረዱ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚመዘኑበት ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ወደ ሥራ ዓለም ሲቀላቀሉ ዳኛ፣ አቃቢ ሕግና ጠበቃ በመሆን ለማኅበረሰቡ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ዜጎች በመሆናቸው በቂ ዕውቀት ጨብጠው መውጣታቸውን መመዘኛ መንገድ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው የሕግ መውጫ ፈተና መሰጠት መጀመሩን የተናገሩት አቶ ጋድሴንድ ትኩረቱም Private የግለሰብመ የማኅበረሰብ፣ የሥነ-ሥርዓትና ልዩ ልዩ ሕጎች ላይ ሆኖ በውስጡ በርካታ የትምህርት ዓይነቶችን የያዘ ነው ብለዋል፡፡ ተማሪዎች ለመመረቅ ይህንን ፈተና ማለፍ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከዚህም ባሻገር ማኅበረሰቡን በመልካም አስተዳደርና ፍትህ አሰጣጥ ለማገልገል ተማሪዎች ተገቢውን ዕውቀት፣ ክሂሎትና ሥነ-ምግባር ይዘው እንዲመረቁና በታማኝነት ሀገርን እንዲያገለግሉ መሰል መመዘኛዎች ጠቃሚ መሆናቸውን አቶ ጎድሴንድ ገልጸዋል፡፡

ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የመጡት አቶ በላይ እንዳሻው እንደገለጹት ፈተናው ወጥ የሆነና በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት እንደ ሀገር የሕግ ትምህርት በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ላሉ የሕግ ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጥ ነው፡፡ ፈተናው የሚዘጋጀው በኤጀንሲው አስተባባሪነት በኢትዮጵያ የሕግ ትምህርት ቤት ካላቸው ዩኒቨርሲቲዎች በተወጣጡ መምህራን ሲሆን እርማቱም በኮድ እንደሚካሄድና ኤጀንሲው በዋናነት ፈተናው አንድ ወጥ ሆኖ መዘጋጀቱን፣ የአሰጣጡን ሂደት፣ እርማቱ በአግባቡ መካሄዱን እንዲሁም የውጤት አሰረጫጨት ሂደቱን እንደሚቆጣጠር አቶ በላይ ተናግረዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት