ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ትምህርት ዘመን በመደበኛ ፕሮግራም ለተመረቃችሁ ተማሪዎች በሙሉ 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለተመረቁ ተማሪዎች ወንድ 3.5 እና ከዚያ በላይ፣ ሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ በ2014 የትምህርት ዘመን ነፃ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል ለ18 ተማሪዎች አወዳደሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የሚትፈልጉ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች ከመስከረም 03-07/2014 ዓ/ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የተማሪዎች ምዝገባና ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እየቀረባችው እንድትመዘገቡ እየገለጽን፡-

         ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች፡-

  • ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁለት(2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት(2) ጉርድ ፎቶግራፍ
  • የድጋፍ ደብዳቤ /Recommendation Letter/
  • በተለያዩ የተማሪ አደረጃጀቶች አገልግሎት የተሰጠበት የምስክር ወረቀት

ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽበት ቀን፡- መስከረም 10/2014 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስከረም 12/2014 ዓ.ም፤

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡-

  • የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ፣ የሕግ ት/ቤት፣ የስነ-ትምህርትና ስነ-ባህሪ ሳይንስ ት/ቤት እና የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አመልካቾች በድኅረ-ምረቃ ት/ቤት ሕንፃ ዋና ግቢ
  • የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ አመልካቾች በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዓባያ ካምፓስ
  •  የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመልካቾች በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነጭ ሣር ካምፓስ
  • የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ አመልካቾች በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ኩልፎ ካምፓስ ይሆናል፡፡
  • የመግቢያ ፈተና ያለፉ አመልካቾችና የምዝገባ ጊዜ በቀጣይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡

 

   አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት