በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በድኅረ ምረቃ ት/ቤት የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ የነበሩት እጩ ዶ/ር ዓለማየሁ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ::  

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ት/ቤት የዴቭሎፕመንት ኢኮኖሚክስ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ የነበሩት እጩ ዶ/ር ዓለማየሁ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ እጩ ዶክተሩ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በግብርና ኮሌጅ በግብርና ቢዝነስ እና እሴት ሠንሰለት ት/ክፍል መምህር የነበሩ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአግሪካልቸራል ሪሶርስ ኢኮኖሚክስ ማኔጅመንት እንዲሁም የ2ኛ ዲግሪያቸውን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በአግሪቢዝነስ እና እሴት ሠንሰለት አስተዳደር አግኝተዋል፡፡
እጩ ዶ/ር ዓለማየሁ አስፋው በድንገት መስከረም 20/2014 ዓ/ም ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በእጩ ዶ/ር ዓለማየሁ አስፋው ድንገተኛ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶችና ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡