የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢንስቲትዩቱ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የ2014 ዓ/ም የመጀመሪያ ዙር የምርምር ንድፈ ሃሳብ ግምገማ መስከረም 14/2014 ዓ/ም አካሂዷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ 

የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉነህ ለማ እንደገለጹት እንደ ምርምር ዩኒቨርሲቲ ለምርምር ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ሲሆን ሁሉም መምህራን ተመራማሪዎች እንዲሆኑ ይበረታታሉ፡፡ ምርምሩን የሚሠሩት ሁሉም የአካዳሚክ ባልደረቦች ሲሆኑ በዚህ ዓመት ሴቶች በዋና ተመራማሪነት ይሳተፋሉ ብለዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲሱ ሙሉጌታ በበኩላቸው እንደ ኢንስቲትዩት ወደ ማኅበረሰቡ ሊሸጋገሩ የሚችሉና ትልቅ ፋይዳ ያላቸው የምርምር ንድፈ ሃሳቦች መገምገማቸውን ተናግረዋል፡፡ ገምጋሚዎቹ የችግሩ ምንነት በትክክል መጠናቱን እንዲሁም የችግሩ መፍትሔ መፈለጊያ መንገድና የሚጠበቀው ውጤት ለመማር ማስተማር ዕውቀት ሽግግር የሚረዳ መሆኑን በትኩረት ገምግመዋል ብለዋል፡፡

የአፈር ጥናት፣ የመሬት መንሸራተት፣ ግንባታ፣ የመንገድ ሥራዎች እና የጋሞኛ ቋንቋ ማስተማሪያ መተግበሪያ ከተገመገሙ የምርምር ንድፈ ሃሳቦች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በዕለቱ 18 የምርምር ንድፈ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያና 2ኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች እና የ5ቱ ፋከልቲ ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

 

       የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት