አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 24/2014 ዓ/ም በተካሄደው 6ኛው ሀገራዊ የመንግሥት ምሥረታ ክቡር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጥዎ የተሰማውን ደስታ እየገለጸ የኃላፊነትዎ ዘመን የኢትዮጵያ ብልፅግና የሚረጋገጥበት፣ የከፍታና የስኬት እንዲሆን በመላው የዩኒቨርሲቲው መኅበረሰብ ስም የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል። 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መንግሥት በሚያስቀምጣቸው የተለያዩ አቅጣጫዎችና በሚቀርጻቸው ፖሊሲዎች ሀገራችን ወደ የበለፀገች፣ ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠና ሠላሟ የተጠበቀ ሀገር እንድትሆን የሚደረገውን ትግል ከመቼውም በበለጠ በምርምር፣ በሠለጠና ሰው ኃይልና በሚያስፈልገው በማንኛውም ሁኔታ ከመንግሥት ጎን የሚቆም መሆኑን በማረጋገጥ ለሀገራችንና ለሕዝባችን የብልፅግና፣ የሠላምና የዕድገት ዘመን እንዲሆን በድጋሚ መልካም ምኞቱን ይገልጻል። መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልዎ!!

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ