የዩኒቨርሲቲው ሁሉ አቀፍ ሴክተር ዳይሬክቶሬት ከአርባ ምንጭ ከተማ ለተወጣጡ በኤችአይቪ/ኤድስ ለተጎዱና አቅም ለሌላቸው 200 ተማሪዎች ጥቅምት 2/2014 ዓ/ም የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የሁሉ አቀፍ ሴክተር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መርክነህ መኩሪያ እንደገለጹት የቁሳቁስ ድጋፉ ከተደረገላቸው ተማሪዎች 40ዎቹ አካል ጉዳተኛ ናቸው፡፡ ተማሪዎቹ በአቅም ውስንነት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ በማሰብ ድጋፉ መደረጉን አቶ መርክነህ ተናግረዋል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ 

አዲስ ተስፋ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ሴቶች ማኅበር ሰብሳቢ ወ/ሮ እቴነሸ እሸቴ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም የምግብ ድጋፍ ማድረጉንና የመኖሪያ ቤት ገንብቶ ለማኅበራቸው አባላት መስጠቱን አስታውሰው ሀገራችን ችግር ውስጥ በወደቀችበትና ድጋፎች በጠፉበት በዚህ ጊዜ ዩኒቨርሲቲው ከጎናቸው በመሆኑ በማኅበሩ ስም አመስግነዋል፡፡

በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ ቴዎድሮስ ዋቤ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማግኘቱ መደሰቱን ገልጾ ዩኒቨርሲቲው መሰል ድጋፎችን ማድረጉ መማር እየፈለጉ አቅም በማጣት ትምህርታቸውን ለሚያቋርጡ ተማሪዎች ብርታት የሚሰጥ ነው ብሏል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት