የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ነባር ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 23-24/2014 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 29/2014 ዓ/ም ይሆናል፡፡

በመሆኑም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም ነባር ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየካምፓሶቻችሁ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ ምዝገባ እንድታካሂዱ እየገለጸ ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት