የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የተቀመጠውን የመግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ አመልካቾችን በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣ በማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በታሪክና ቅርስ አስተዳደር፣ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ - አማርኛ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ፣ በሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ጥናት፣ በሶሾሎጂና ሶሻል አንትርፖሎጂ እና በፒጂዲቲ ትምህርቶች በአርባ ምንጭ፣ በአዲስ አበባ፣ በሳውላ፣ በምዕራብ ዓባያ፣ በካምባ፣ በቁጫ፣ በኮንሶ፣ በባስኬቶ እና በአማሮ ኬሌ ልዩ ወረዳዎች ማዕከላትን ከፍቶ በመጀመሪያ ዲግሪ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡

  • የምዝገባ ቀን ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 30/2014 ዓ.ም
  • ·የመመዝገቢያ ቦታ:-
  •  በአዲስ አበባ፤ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ አራት ኪሎ
  • በአርባ ምንጭና ሳውላ፤ በነጭ ሳር እና ሳውላ ካምፓሶች የተከታታይና ርቀት ት/ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች
  • በተቀሩት ከተሞች የመሰናዶና 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-181-4512/0913-425-332/0942-234-515 በመደወል ወይም ከዩኒቨርሲቲዉ ድረ-ገጽ /www.amu.edu.et/፣ ቴሌግራምና ፌስቡክ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ