መ/ር መቆያ መርጊያ ከአባታቸው ከአቶ መርጊያ በላይነህ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አባይነሽ አራጫ በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ገረሴ ከተማ ግንቦት 14/1983 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በጊዶሌ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጊዶሌ 2ኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በውሃ ሀብትና መስኖ ምኅንድስና ሰኔ 9/2007 ዓ/ም የተቀበሉ ሲሆን 2ኛ ዲግሪያቸውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሃይዲሮሊክ ምኅንድስና ነሐሴ 25/2012 ዓ/ም አግኝተዋል፡፡

ከመጋቢት 5/2008 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በውሃ ሀብትና መስኖ ምኅንድስና ት/ክፍል በረዳት ሌክቸረር እንዲሁም ከነሐሴ 25/2012 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ሌክቸረር አካዳሚክ ማዕረግ በማደግ ሕይወታቸው እስካለፈችበት ቀን ድረስ አገልግለዋል፡፡

መ/ር መቆያ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ31 ዓመታቸው ጥቅምት 19/2014 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመ/ር መቆያ መርጊያ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት