የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2014 የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅትና በ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ዙሪያ ጥቅምት 20/2014 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉነህ ለማ በትምህርት ዘመኑ ዕቅዶች፣ ቅድመ ዝግጅቶችና ተግዳሮቶች ላይ ከመምህራን ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ሁሉም መምህራን የአሠራር ደንቦችን በአግባቡ በመረዳትና ጉድለቶችን በማሻሻል ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰሎሞን ንዋይ በበኩላቸው ባለፉት የትምህርት ዓመታት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የሥራ መደራረቦችና ጫናዎች እንደነበሩ ገልጸው በቀጣይ ጊዜያትም የተሻለ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት መምህራንና አመራሩ ሙሉ ኃላፊነትን ወስደው ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በውይይቱ የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክና ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች፣ ዲኖች፣ አስተባባሪዎችና መምህራን ተሳትፈዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት