አርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከAMU-IUC ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለአምስቱ ፋከልቲ ዲኖች፣ ኃላፊዎች፣ አስተባባሪዎችና መምህራን በፕሮጀክት ንድፈ-ሃሳብ ዋና ዓላማዎችና አዘገጃጀት ላይ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የኢንስቲትዩቱ ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰሎሞን ንዋይ እንደገለጹት የኢንስትቲዩቱ የፕሮጀክት ንድፈ-ሃሳብ ዝግጅት ተሳትፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ ነው፡፡ ችግሩን ለመቅረፍና ከመንግሥት የሚመደበውን የምርምር በጀት ብቻ ከመጠበቅ ይልቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና አሸናፊ በመሆን ተማሪዎችና መምህራን የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንዲሁም የማኅበረሰብ አገልግሎትን በምርምር ተደራሽ ለማድረግ ሥልጠናው ተዘጋጅቷል፡፡ የምርምር ንድፈ ሃሳብ መሠረታዊ ነገሮች፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችና ከዩኒቨርሲቲው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በሥልጠናው መዳሰሳቸውን ዶ/ር ሰሎሞን ተናግረዋል፡፡

የAMU-IUC ፕሮግራም አስተባባሪና አሠልጣኝ ዶ/ር ፋሲል እሸቱ የፕሮጀክት ንድፈ-ሃሳብ አሠራር እና ከውጭ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የሚቻልበት መንገድ ላይ ሥልጠናው መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ አዲስ ፕሮጀክቶችን ለመቅረፅ በቂና ሁሉን አካታች ንድፈ ሃሳብ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ያሉት ዶ/ር ፋሲል ይህም የግል ጥረትን በእጅጉ የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት