የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕ ጽ/ቤት ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የሆኑ አማራጭ የኃይል ቴክኖሎጂዎችን ለማኅበረሰቡ በጋራ በማዳረስና በሌሎች የትብብር ሥራ አማራጮች ዙሪያ መጋቢት 16/2014 ዓ/ም ውይይት ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በውይይቱ ወቅት እንደተመለከተው “Vita” በ1989 ዓ/ም በአየርላንድ የተመሠረተ የልማትና የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ድርጅቱ በዋናነት በአፍሪካ ውስጥ ድህነትን ለማጥፋትና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮችን ለመከላከል የሚሠራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ደርጅቱ “Vita Green Impact Fund” በተሰኘ ፕሮግራሙ በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ለሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተስማሙ የኃይል አማራጮችን በማቅረብ ላይ እየሠራ ያለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በመስኩም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር የመሥራት ፍላጎት እንዳለው ልዑክ ቡድኑ ገልጿል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ከላይ በተገለጸው መሠረት የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በቅርቡ እንደሚፈራረሙ ዕቅድ ይዘዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት