Print

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ በ2014 የትምህርት ዘመን ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ፡-

የተወሰኑት በምደባቸው መሠረት ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን እስከ አሁን ሪፖርት ያላደረጋችሁ ለመጨረሻ ጊዜ ምዝገባ የሚካሄደው ሚያዝያ 19-20/2014 ዓ/ም ሆኖ መደበኛ ትምህርት የሚጀመረው ሚያዝያ 21/2014 ዓ/ም መሆኑን ይገልጻል፡፡ ጉዳዩ የሚመለከታችሁ የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በዩነቨርሲቲው ዋናው ግቢ በሚገኘው የዩነቨርሲቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 210 እና 211 በአካል ቀርባችሁ ምዝገባ እንድታካሂዱ ጥሪውን እያስተላለፈ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በአጽንኦት ያሳውቃል፡፡

ማሳሰቢያ፡- በነባር ዩኒቨርሲቲያችሁ ባላችሁበት ጊዜ የኮርስ ሥራ አጠናቅቃችሁ ከአማካሪ ጋር የድኅረ-ምረቃ ማሟያ ምርምር ሥራ የጀመራችሁ የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ከአማካሪያችሁ ጋር መቀጠል የሚትችሉ ሲሆን፤ ነገር ግን አማካሪያችሁ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጊዜያዊነት መጥቶ በጋራ ለመሥራት ፈቃደኛ መሆኑን ለምዝገባ ከመምጣታችሁ በፊት ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት