ተማሪ ዳዊት ጥላሁን ከአባቱ ከአቶ ጥላሁን አያኖ እና ከእናቱ ከወ/ሮ መብራት ደቻሳ ጥቅምት 27/1989 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ከተማ ተወለደ፡፡ ተማሪ ዳዊት የ1ኛ ደረጃ ትምህርቱን በጫሞ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት እና የፕሪፓራቶሪ ትምህርቱን በጫሞ ሁለተኛ ደረጃና መሠናዶ ት/ቤት ተከታትሏል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ተማሪ ዳዊት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሰርቬይንግ ምኅንድስና ፋከልቲ የ5ኛ ዓመት ትምህርቱን እየተከታተለ ያለ ሲሆን የፋሲካ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር ለማሳለፍ ከግቢ ወጥቶ ባለበት ሚያዝያ 18/2014 ዓ/ም ድንገተኛ ኅልፈተ ሕይወቱ ተሰምቷል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተማሪው ድንገተኛ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለፋከልቲው መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት