በ2014 የትምህርት ዘመን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 1 እና 2 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 3 እና 4 እንዲሁም ትምህርት የሚጀመረው ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ይሆናል፡፡

በመሆኑም ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡- 

  •  የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና ኮፒ፣
  • ከ9ኛ-12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና ኮፒ፣
  • የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጂናልና ኮፒ፣
  •  አራት ፓስፖርት ሳይዝ የሆነ ጉርድ ፎቶ፣
  • አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፣ እንዲሁም
  • ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ)

በመያዝ ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ ካምፓሶች የተመደባችሁ በየካምፓሶቻችሁ በሚገኙ የሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን የተመደባችሁበት ካምፓስ መረጃ ከዩኒቨርሰቲው ድህረ-ገጽ www.amu.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንዲሁም ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡

      የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት