Print

በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ስር በሚገኙ ሚቲዎሮሎጂ እና ሀይድሮሎጂ ፋከልቲዎች በቀረቡ 2 የሦስተኛ ዲግሪና 1 የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ሰኔ 6/2014 ዓ/ም የውጭ የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ፕሮግራሞቹ ‹‹PhD in Climate Change and Sustainable Development››፣ ‹‹PhD in Meteorology›› እና ‹‹ MSc in Geoinformation and Earth Observation for Hydrology›› መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር አብደላ ከማል ገልጸዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የሚሠሩ የምርምር ጽሑፎች ለሀገር እንዲጠቅሙ በማድረግ ከጥናቶች ግብዓት በመውሰድ ለተግባራዊነታቸው አጽንኦት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ዶ/ር አብደላ ተናግረዋል፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞችን ቁጥር በስፋትና በጥራት እየጨመረ መሄድ የሚጠበቅበት ሲሆን የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትም የዩኒቨርሲቲውን የትኩረት አቅጣጫ ተከትሎ የ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ቁጥር ለማሳደግ እየሠራ ነው፡፡ አዲስ በሚከፈቱት የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ከኢትዮጵያ ባሻገር ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ለመቀበል ጭምር እንዲያቅዱም ም/ፕሬዝደንቱ ጠቁመዋል፡፡

ፕሮግራሞቹ በከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ መሠረት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የውስጥ ግምገማ የተደረገባቸው ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ተቋማዊ ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት አግባብነታቸው ተረጋግጦ ለውጭ ግምገማ ቀርበዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት