የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት  መጨረሻ  መርሃ  ግብሮ  መስፈርቱን  የሚያሟሉ  አዲስ  አመልካቾችን ከዚህ  በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡ የፕሮግራሞችን ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ

ምዝገባው የሚከናወነው በመረጃ መረብ/ Online/ ከታች የቀረበውን ሊንክ በመጫን/በድረ-ገጽ ላይ ኮፒ-ፔስት በማድረግ/ መጠይቆችን ባግባቡ በመሙላትና የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በማያያዝ ሲሆን ያልተሟሉ መረጃዎች ያሏቸውን አመልካቾች የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን

https://forms.gle/J4o1bsAxzyGtPaYJ6 

የመግቢያ ፈተናውን ያለፉ ተመዝጋቢዎች በአካል ማቅረብ የሚጠበቅባቸው መረጃዎች

1.የትምህርት መረጃ፡- ሙሉ የትምህርት መረጃ  ኦሪጅናልና ሁለት(2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት(2) ጉርድ ፎቶግራፍ

2.የድጋፍ ደብዳቤ፡- የአመልካቹን ጥንካሬና ባህሪ የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከመ/ቤት  ኃላፊ  /ከቀድሞ መምህር/ Recommendation Letter/

3.የመመዝገቢያ ክፍያ፡- የማመልከቻ ክፊያ የ100 ብር ገቢ የተደረገበትን የባንክ ስሊፕ ወደ ደረሰኝ በማስቀየር፣ ደረሰኝ በመያዝ፣ የማመልከቻ ቅጽ በመሙላትና በማቅረብ (የማመልከቻ ቅጽ ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣
   211 እና ከዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዩኒቨርሰርሲቲው አካውንት ቁጥር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000021480502 መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

4. በመንግስት/በድርጅት ስፖንሰርነት ለሚማሩ በመሥሪያ ቤቱ/በድርጅቱ ኃላፊ የተፈረመ ስፖንሰርሺፕ ደብዳቤና /Sponsorship form/ (ፎርሙን ቀደም ብለው ከዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ ማግኘት ይችላሉ) ማቅረብ
    ይጠበቅባቸዋል፡፡

የፈተና መስጫ፣  የውጤት ማሳወቂያ፣ የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ

የማመልከቻ ጊዜ፡- ከሐምሌ18/2014 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 27/2014  ዓ.ም፤

ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር የሚወጣበት ቀን፡- ጳጉሜ 01 - 03/2014 ዓ.ም፤ ለፈተና  ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ (www.amu.edu.et) መከታተል ይችላሉ፡፡

የመግቢያ ፈተና  የሚሰጥበት  ቀን፡-  መስከረም 5/2015  ዓ.ም

 ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡- 

1.የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች፣ የማኅበራዊ ሳይንስ፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ የሕግ እና
    የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ተማሪዎች - ዋናው ግቢ

2.የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ነጭ ሳር ካምፓስ

3.የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ዓባያ ካምፓስ

4.የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ኩልፎ ካምፓስ

5.የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች - በሳዉላ ካምፓስ

ማሳሰብያ፡-

  • መደበኛ የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ሁሉም በተመጣጣኝ ክፊያ የዶርም አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
  • 3 ዲግሪ ተማሪዎች ምርምራቸውን የሚያካሂዱበት በዩኒቨርሲቲው ምርምር መመሪያ መሠረት የፋይናንስ ድጋፍ ይደረጋል::
  • ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት/Official Transcript/ ቢቻል በምዝገባ ወቅት ካልሆነ በ60 ቀናት ውስጥ ካላቀረበ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

                የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አ/ዳ/ጽ/ቤት