Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል ከዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ ጉድኝትና ከተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬቶች እንዲሁም ከ STEMpower መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር ከጋሞ፣ ጎፋና ኮንሶ ዞኖች እና ከደራሼ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂና አማሮ ልዩ ወረዳዎች ለተወጣጡ 291 ከ7-12 ክፍል ተማሪዎች በኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ሒሣብ፣ ኤሌክትሮኒክስና ICT ትምህርቶች ከሐምሌ 15 - ነሐሴ 30/2014 ዓ/ም የሚቆይ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ተማሪዎች በየሚማሩባቸው ት/ቤቶች ምቹ የመማር ማስተማር ሂደት ባይኖርም በዕውቀት፣ በአስተሳሰብና በአመለካከት እንዲያድጉ እንዲሁም በቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ ብቁ እንዲሆኑ በማለም ሥልጠናው ተዘጋጅቷል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት