Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ዩኒቨርሲቲውን በሚቀጥሉት 6 ዓመታት በፕሬዝደንትነት የሚመራውን ኃላፊ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የአመልካቾች ትምህርት ደረጃ ሁለተኛ ዲግሪ (ማስትሬት) ከረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ጋር እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.Curriculum Vitae (CV)
2.የትምህርት ደረጃን የሚገልጽ ሰርተፊኬት አንድ ፎቶ ኮፒ፤
3.የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገልጽ ደብዳቤ፤
4.በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ወይም በምርምር ተቋም በተመራማሪነት ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ፤
5.በዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉበትን የሚገልጽ ደብዳቤ፤
6.በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንትነት ቢመደቡ የዘርፉን ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ በዝርዝር ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡

ከላይ በተገለጸው መሠረት ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ከነሐሴ 23 እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት በዋናው ግቢ አስተዳደር ሕንጻ በቢሮ ቁጥር 209 በአካል ቀርባችሁ ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ