የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ለአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የአመልካቾች ትምህርት ደረጃ 2ኛ ዲግሪ (ማስትሬት) ከረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ጋር እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.Curriculum Vitae (CV)
2.የትምህርት ደረጃን የሚገልጽ ሰርተፊኬት አንድ ፎቶ ኮፒ
3.የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገልጽ ደብዳቤ
4.በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ወይም በምርምር ተቋም በተመራማሪነት ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ
5.በዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉበትን የሚገልጽ ደብዳቤ
6.በኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተርነት ቢመደቡ የዘርፉን ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ በዝርዝር ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡

ከላይ በተገለጸው መሠረት ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ከነሐሴ 23 እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት በዋናው ግቢ አስተዳደር ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 209 በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን አናስታውቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ