አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለተመረቁ ተማሪዎች ወንድ 3.5 እና ከዚያ በላይ፣ ሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ በ2015 የትምህርት ዘመን ነፃ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል ለ18 ተማሪዎች (AMIT 2፣ AWTI 2፣ CBE 2, CSSH 2, CMHS 2, CAS 2, CNS 2, School of Law 1, school of PBS 1, Sawula campus 2)  አወዳደሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የሚትፈልጉ የ2014 ተመራቂ ተማሪዎች ( መስከረም 29/30 እና ሰኔ 25/26 2014 ዓ.ም የተመረቃችሁ) ከነሐሴ 18-27/2014 ዓ/ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት እንድትመዘገቡ እየገለጽን፡-


ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች፡-
1. ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁለት(2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት(2) ጉርድ ፎቶግራፍ
2.  የድጋፍ ደብዳቤ /Recommendation Letter/
3.  በተለያዩ የተማሪ አደረጃጀቶች አገልግሎት የተሰጠበት የምስክር ወረቀት
4. የማመልከቻ ቦታ፡- የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የተማሪዎች
    ምዝገባና ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211
5.  ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽበት
     ከጳጌሜ1-3/2014 ዓ.ም
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስከረም 5/2015 ዓ.ም፤
ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡-
1. የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች፣ የማኅበራዊ ሳይንስ፣ የቢዝነስና  
   ኢኮኖሚክስ፣ የሕግ እና የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ተማሪዎች - ዋናው ግቢ
2. የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ነጭ ሳር ካምፓስ
3. የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ዓባያ ካምፓስ
4. የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ኩልፎ ካምፓስ
5. የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች - በሳዉላ ካምፓስ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት