በዩኒቨርሲቲው የሥልጣን ዘመናቸውን ያጠናቀቁትን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የሚተኩ አመራሮችን አወዳድሮ ለመመደብ የእጩ መልማይና የምልመላ ኮሚቴ አባላት
ነሐሴ 16/2014 ዓ/ም ተመርጠዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጄኔራልና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ፈጠነ ተሾመ እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲውን ሥራ አመራር ቦርድ፣ ሴኔት፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራኞችና ተማሪዎችን የሚወክሉ አምስት አባላትን ያቀፈ የምልመላና የመራጭ ኮሚቴ ተደራጅቷል፡፡

በዚህም መሠረት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድን በመወከል አቶ ፈጠነ ተሾመ፣ ከመምህራን ኅብረት አቶ ጋሻው ዓለሙ፣ ከሴኔት አቶ አንለይ ብርሃኑ፣ ከአስተዳደር ሠራተኞች ወ/ሮ ከአምላክነሽ ደሳለኝ እና ከተማሪዎች ኅብረት ተማሪ ደሳለው ቆለጭ የእጩ መልማይና የምልመላ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡

የተዋቀረው ኮሚቴ ማስታወቂያ ከማውጣት ጀምሮ ምርጫው በመመሪያው መሠረት መከናወኑን እየተከታተለ መልዕክቶችን ለቦርዱ የሚያቀርብ ሲሆን ቦርዱ ለትምህርት ሚኒስቴር በመላክ የሚያስፀድቀው ይሆናል፡፡

በውድድሩ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ከነሐሴ 23 እስከ ጳጉሜ 4/2014 ዓ/ም ዘወትር በሥራ ሰዓት በዋናው ግቢ አስተዳደር ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 209 በአካል ቀርበው ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት