Print

አቶ ዮናስ አስፋው ከአባታቸው ከአቶ አስፋው ማዳ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለች ቦርቾ በቀድሞው ጋሞ ጎፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ በ1981 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን ከአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት በ‹‹Vehicle Servicing and Repairing›› በደረጃ II ተመርቀዋል፡፡

አቶ ዮናስ ኅዳር 1/2003 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኮንትራት ቅጥር ፈጽመው እስከ የካቲት 30/2005 ዓ/ም በሾፌር ረዳትነት ያገለገሉ ሲሆን ከመጋቢት 1/2005 ዓ/ም ጀምሮ በቋሚነት እስከ ታኅሣሥ 15/2006 ዓ/ም የይዞታ ልማት የመገ/መሳ/ዳይሬክቶሬት ሾፌር፣ ከታኅሣሥ 16/2006 - ታኅሣሥ 30/2006 ዓ/ም የመለስተኛ መኪና ሾፌር፣ ከጥር 1/2009 - ነሐሴ 30/2010 ዓ/ም ሾፌር II እንዲሁም ከመስከረም 1/2011 ዓ/ም ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በደረጃ VI በሾፌርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ ዮናስ ባለ ትዳር ሲሆኑ ነሐሴ 21/2014 ዓ/ም በተወለዱ በ33 ዓመታቸው በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአቶ ዮናስ አስፋው ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት