Print

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲሱን ዓመት በማስመልከት ለአረጋውያን፣ ለአቅመ ደካሞች፣ በተለያዩ  ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ላጡና ለዘማች ቤተሰብ አባላት በድምሩ ለ115 አባወራዎች ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ግራም በድምሩ 29 ኩንታል የሚሆን የፉርኖ ዱቄት ለማዕድ ማጋራት እንዲውል ለአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 03/2014 ዓ/ም አስረክቧል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን 150 ሺ ብር የሚጠጋ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በጎ ተግባር ለማከናወን ድጋፉ የሚያስፈልጋቸውን 1000 ሺህ የሚጠጉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ወጥ በሆነ መልኩ በአንድ ቋት ማዕድ ለማጋራት እንዲቻል በጋራ ለመሥራት ከከተማው አስተዳደር በቀረበው ጥያቄ መሠረት ዩኒቨርሲቲው ድጋፉን ማስረከቡ ተገልጿል፡፡

 ከተለያዩ ዘርፎች በአንድ ቋት የተሰበሰበው ድጋፍም በከተማው አስተዳደር አማካኝነት ከጳጉሜ 04/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሚመለከታቸው ወገኖች እንደሚከፋፈል ተጠቁሟል፡፡

 የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት