Print

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ለተመራቂ ተማሪዎች የፊታችን ሐሙስ መስከረም 05/2015 ዓ/ም ከቀኑ 08፡00 – 11፡30 በኩልፎ ካምፓስ፣ ዓርብ መስከረም 6/2015 ዓ.ም ከጧቱ 2፡00 – 06፡30 በቴክኖሎጂና በውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች እና ከሰዓት ከ08፡00 – 11፡30 በዓባያ ካምፓስ እንዲሁም ሰኞ መስከረም 9/2015 ዓ/ም ከጧቱ 2፡00 – 06፡30 በነጭ ሳር ካምፓስ በሥነ-ምግባርና ሞራል ዕሴቶች ግንባታ እና ብልሹ አሠራርን በመከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ሥልጠና በዋናው ግቢ በቴክኖሎጂ ትልቁ አዳራሽ እና በካምፓሶች በተማሪዎች መመገቢያ አዳራሾች የሚሰጥ ስለሆነ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ በመገኘት ሥልጠናውን እንድትወስዱ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ሥልጠናውን በሚገባ ተከታትለው ላጠናቀቁ ተማራቂዎች የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በመልካም ሥነ-ምግባር የሚሰጥ አገልግሎት ከሙስና ለፀዳ ተቋም!!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት