ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከአንድ ሺህ በላይ የ35 ባች የሕክምናና ጤና ሳይንስ፣ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ፣ የግብርና እና የምኅንድስና ተማሪዎች መስከረም 12/2015 ዓ/ም ለ2 ዙር ያስመርቃል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 464ቱ ሴቶች ናቸው፡፡

የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በዋናው ግቢ ትልቁ አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 25 እና 26/2014 ዓ/ም የመጀመሪያውን ዙር በአርባ ምንጭና ሳውላ ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት