Print

አቶ ሙሉነህ መንገሻ ከአባታቸው ከአቶ መንገሻ ቃንኤ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዓለሚቱ በላቸው በቀድሞ በሰሜን ኦሞ ዞን በጋሞ አውራጃ በቁጫ ወረዳ መስከረም 12/1958 ዓ.ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ በጎፋ ወረዳ በገልጣ ከተማ  1- 6 ክፍል በገሪማ 1 ደረጃ ት/ቤት፣ ከ7- 8 ክፍል በአርባ ምንጭ ከተማ በኩልፎ ሙሉ 1 ደረጃ ት/ቤት እና ከ9- 10 ክፍል  የ2 ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ  2 ደረጃ  ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡

አቶ ሙሉነህ መንገሻ ከየካቲት 17/1986 - ሚያዝያ 11/1991 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኮንትራት ቅጥር በጥበቃ ሠራተኛነት፣ ከታኅሳስ 3/1992 ዓ.ም - ግንቦት 30/1995 ዓ.ም በቋሚ ቅጥር በአትክልተኛነት፣ ከሰኔ 1/1995 - ነሐሴ 30/2005 ዓ/ም በቋሚ ቅጥር በአ/ም/ዩ ፖሊስነት፣ ከጳጉሜ 1/2005 - ሰኔ 30/2010 ዓ/ም በዋናው ግቢ የተማሪዎች መኝታ አገልግሎት ሠራተኛነት፣ ከሐምሌ 1/2010 እስከ ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የቤተ-መፅሐፍትና መረጃ አገልግሎት ሠራተኛ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር፡፡

አቶ ሙሉነህ መንገሻ ባለትዳርና የሁለት ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ በደረሰባቸው ድንገተኛ ሞት በተወለዱ በ57 ዓመታቸው መስከረም 11/2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ሙሉነህ መንገሻ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለጓደኞቻቸውና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት