ትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ብሔራዊ  ፈተና  አሰጣጥ ሂደት  ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከቱ የፀጥታ አካላት፣ የትምህርት ቢሮዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎችና እና ሌሎች ተቋማት የምስጋናና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል። ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም በሀገር ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች የተሰጠው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ ከሁሉም ባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት ላደረገው አበርክቶ የምስጋናና የዕውቅና ምስክር ተሰጥቶታል።

በዚሁ አጋጣሚ ዩኒቨርሲቲው ለፈተናው በሰላም መጠናቀቅ የሁሉም ባለድርሻዎች ሚና የጎላ በመሆኑ ምስጋናውን እያቀረበ በተሰጠው ዕውቅና የተሰማውን ደስታ ይገልጻል።

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት