Print

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከጋሞ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያና ደረጃ ዶት ኮም/Dereja.Com/ ከተሰኘ የግል ድርጀት ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ  ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2013  እና 2014 ዓ/ም ተመርቀው ሥራ በማፈላለግ ላይ ለሚገኙ ወጣቶች በሥራ ዝግጁነት /Job Readiness/ ዙሪያ ኅዳር 7/2015 ዓ/ም  ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዴሊቨሮሎጂ ዩኒት ዲን ዶ/ር ጌታነህ ተስፋዬ  በዩኒታቸው ስር የሚገኘው የሙያ ማበልጸጊያ ማዕከል/Career Center/ ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ከሚያገኙት ቴክኒካል ዕውቀት በተጨማሪ ለሥራ ፈጣሪነትና ሥራ ለማግኘት የሚያስችሉ ሥልጠናዎችን ሲሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  የዕለቱ ሥልጠናም በአርባ ምንጭ ከተማ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች  ተመርቀው ሥራ በማፈላለግ ላይ ለሚገኙ 580 ወጣቶች  ከጋሞ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያና ከደረጃ ዶት ኮም ጋር በመተባበር የተዘጋጀና ወጣቶቹን ለሥራ ፈጣሪነትና ተቀጣሪነት ዝግጁ የሚያደርጉ ግንዛቤዎችን ለመፍጠር የተዘጋጀ ነው፡፡

የጋሞ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት  መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉዓለም በየነ ሥልጠናው ወጣቶቹን የሥራ ፈጣሪነትና ዝግጁነት አቅምን የሚያጎለብትና ቀጣሪ ተቋማት የሚፈልጉትን ክሂሎት ለማስገንዘብ የሚያግዝ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ 

የደረጃ ዶት ኮም ሪጂናል ማኔጀርና አሠልጣኝ በእምነት ለጥይበሉ ሥልጠናው የሥራ ዝግጁነት /Job Readiness/ በሚል ርዕስ ድረስ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው በተለያዩ ምክንያቶች ሥራ ያልፈጠሩና ያልያዙ ወጣቶችን ወደ ሥራ ዓለም ለማስገባት የሚያግዙ ክሂሎቶችን ለማስገንዘብ የተዘጋጀ ነው፡፡ ተቋማቸው መሰል ሥራዎችን ከ12 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየሠራ መሆኑን የጠቀሱት አሠልጣኟ የዚህ ዓይነት ሥልጠናው በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ለሚገኙ ወጣቶችም የሚሰጥ መሆኑን አሠልጣኟ ጠቁመዋል፡፡

ከሠልጣኞች መካከል ወጣት ወንድማገኝ ታደሰ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በኮንስትራክሸን ማኔጅመንት ቴክኖሎጂ በ2013 ዓ/ም የተመረቀ ሠልጣኝ ሥልጠናው ከ ‹‹CV›› አዘገጃጀት ጀምሮ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ራስን መግለጽ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ የፈጠረ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በሥልጠናው የተገኙ ግንዛቤዎች ሥራ ለመፍጠርም ሆነ ለማግኘት የሚያስችሉ አሠራሮችን የተገነዘበበት መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

 የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት