በማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ እና በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች የምርምር ማስ/ጽ/ቤቶች አማካኝነት 85 የምርምር  ንድፈ ሃሳቦች ቀርበው  ከኅዳር 9-10/2015 ዓ/ም ተገምግመዋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የምርምር ማስ/ጽ/ቤት አስተባባሪ ዶ/ር እንዳልካቸው ኃይሉ እንደገለጹት ንድፈ ሃሳቦቹ  ትኩረት ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የምርምር ማዕቀፍ በሆኑት በደቡብ ክልል በሚገኙ ዞኖች ችግር ፈቺ ምርምሮችን ለማካሄድ ነው፡፡ በመሆኑም በኮሌጁ ውስጥ ከሚገኙ 7 የትምህርት ክፍሎች 40 መምህራን ንድፈ ሃሳቦቻቸውን አቅርበው መገምገማቸውን አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡ በግምገማው ውጤት መሠረት የማኅበረሰቡን ችግር የሚፈቱ፣ ሳይንሳዊ የሆኑ፣ ከዚህ በፊት ያልተሠራባቸውንና መስፈርቱን የሚያሟሉ የጥናት ንድፈ ሃሳቦች ለምርምር እንደሚያልፉ

የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ አካዳሚክ ዳይሬክተርና የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ተወካይ ረ/ፕ ተክሉ ተሾመ በበኩላቸው የንድፈ ሃሳቡ ግምገማ ዓላማ የምርምሩን አዲስነት በመመልከት በሕክምናና ጤና ዘርፍ የተዘጋጁት ንድፈ ሃሳቦች ለዓለም፣ ለሀገርና ለአከባቢው ማኅበረሰብ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ተገምግሞና ተለይቶ ወደ ትግበራ ለማስገባት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሕክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምር ማስ/ጽ/ቤት ኃላፊ ረ/ፕ ምስጉን ሸዋንግዛው በበኩላቸው ከግምገማው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በመውሰድ  የማኅበረሰቡን ችግር ለመፍታትና መፍትሄ ለማምጣት የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው ፕሮግራሙ    ሁሉንም የትምህርት ክፍሎች ያሳተፈ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም  ከኮሌጁ 84 የምርምር ንድፈ ሃሳቦች ቀርበው አስፈላጊ  45ቱ  ለግምገማ ማለፋቸውን ጠቁመዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ በማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ለግምገማ ከቀረቡ ንድፈ ሃሳቦች መካከል ‹‹Academic Writing Problem of Graduate Students: Supervisee and Supervisors perspectives››፣ ‹‹Agenda Setting Role of the State Media in Ethiopia EBC and Debub TV in Focus››፣ ‹‹Faculty Perception and Use of ICT for Professional Development፡ Selected Public University in Focus››፣ “Currents Trends and Challenges of Research and Academic Publishing in Ethiopia Public Universities›› የሚጠቀሱ ሲሆን ‹‹Disease Patients Who have Follow Up at Hospitals of Arba Minch Town and Surrounding Areas, Southern Ethiopia, 2022››፣ “Prevalence of Burnout and Associated Factors Among Nurses working in public Hospitals of Gamo Zone, Southern Ethiopia. A Multi–center Crosssectional Study›› እና ‹‹Health Related Quality of Life and Its Associated Factors among Rheumatic Heart›› በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለግምገማ ከቀረቡ ንድፈ ሃሳቦች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት