Print

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ‹‹iCog Anyone Can Code›› ከተሰኘ ድርጅት፣ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከሁዋዌ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ ካሉ ልማት፣ ጫሞ፣ ዓባያና አርባ ምንጭ 2 ደረጃና መሠናዶ ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ከታኅሣሥ 20 - ጥር 5/2015 ዓ/ም የሚቆይ ዲጂትረክ/ DigiTruck/ በተሰኘ ፕሮጀክት የአይ ሲ ቲ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ሥልጠናው ታዳጊ ተማሪዎች በኮዲንግ፣ ፕሮግራሚንግ፣ ሮቦቲክስና ሌሎች አዳዲስ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ከጽንሰ ሃሳብ ያለፈ ተጨባጭ ተሞክሮ እንዲኖራቸውና የቴክኖሎጂውን ዓለም እንዲተዋወቁ የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም ታዳጊዎች ያላቸውን ተነሳሽነት፣ ትኩረት፣ የማገናዘብ፣ የችግር ፈቺነት እና የፈጠራ ክሂሎት ዝንባሌን በእጅጉ እንዲያሳድጉ የሚያደርግ ነው፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን፣ የኮሌጁ የማኅበረሰብ ጉድኝት አስተባባሪ፣ የት/ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራንና የ‹‹ICT›› መምህራን እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡  

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት