Print

‹‹በሀገር ግንባታ ላይ የምሁራን ሚና›› በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው ካውንስል እና መምህራንና የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች ከታኅሣሥ 24-27/2015 ዓ/ም የሚቆይ ሀገራዊ ውይይት እያካሄዱ ይገኛል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ታኅሣሥ 24/2015 ዓ/ም በጧቱ መርሃ-ግብር ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል ውይይት መነሻ ሠነድ ቀርቦ የካውንስል አባላት በሠነዱ ዙሪያ ሰፊ የውይይት ጊዜ እንዲኖራቸውና ሃሳባቸውን የማጋራት ዕድል እንዲያገኙ እስከ ታኅሣሥ 25/2015 ዓ/ም የጧቱ መርሃ-ግብር ድረስ በቡድን ውይይት ላይ እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ ከቡድን ውይይቱ ቀጥሎም በከሰዓት በኋላ መርሃ-ግብር የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢና የኢፌዴሪ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንትና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከካውንስል አባላት በቡድን ውይይቶች በተነሱ ዋና ዋና ሃሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ዙሪያ ማብራሪያዎችና ገለጻዎች ቀርበው ተጠቃሏል፡፡  

የመምህራንና የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች የውይይት መርሃ-ግብር ታኅሣሥ 26/2015 ዓ/ም ሀገራዊ ሠነዱን በማቅረብ የተጀመረ ሲሆን ታኅሣሥ 26/2015 ዓ/ም ከሰዓት ጀምሮ እስከ ዛሬ ጧት ድረስ በአምስት ቡድኖች የቡድን ውይይት እየተካሄደ ቆይቷል፡፡ በቡድን ውይይቶች ወቅት የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች ተይዘው ዛሬ ከሰዓት ሁሉም ቡድኖች በሚገናኙበት የጋራ መድረክ ላይ አስፈላጊ ማብራሪያዎችና ገለጻዎች የሚደረጉ ይሆናል፡፡

ለአራተኛ ቀን በዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት በማድረግ እየተካሄደ የሚገኘው ሀገራዊው የምሁራን ውይይት በሰላማዊና በዲሞክራሲያዊ ሁኔታ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተሬት