Print

ዕጩ ዶ/ር አሸናፊ ኃይሉ የ3 ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፉን የውስጥና የውጭ ገምጋሚዎች በተገኙበት ጥር 03/2015 ዓ.ም አቅርቧል፡፡

ዕጩ ዶ/ር አሸናፊ ያቀረበው የመመረቂያ ጽሑፍ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአየር ንብረት ለውጥ፣ በምግብ ዋስትናና በገጠር አኗኗር መተዳደሪያ ዕቅድ ዙሪያ “Climate Variability, Smallholder Rural Households’ Economic Base and Food Security Status in North Shewa, Oromia Region, Ethiopia” በሚል ርዕስ ላይ የተከናወነ ነው፡፡ ተጨማሪ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር አሸናፊ የሁለት የመጀመሪያ እና የሁለት ማስተርስ ዲግሪዎች ባለቤት ሲሆን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ“Bachelor of Education in History” እና  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ“Bachelor of Arts Degree in Economics” የመጀመሪያ ዲግሪዎቹን እንዲሁም ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ“Disaster Risk Science & Sustainability Development” እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ“Master Arts Degree in History” የ2 ዲግሪ ትምህርቱን አጠናቋል፡፡  ዕጩ ዶ/ር አሸናፊ የ3 ዲግሪውን ትምህርት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ“Disaster Risk Management” ትምህርት መስክ በስኬት ተከታትሎ በማጠናቀቅ የመመረቂያ ጽሑፍ ያቀረበ ሲሆን የመመረቂያ ጽሑፉም በአማካሪ ቦርዱ ተገምግሞ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡

ዕጩ ዶ/ር አሸናፊ 3 ዲግሪውን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሲያጸድቅ የሚሰጠው መሆኑ ተገልጿል፡፡ 

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት