በ‹‹AMU-IUC›› ፕሮግራም 4ው ፕሮጀክት በሲሌ እና ሻፌ ንዑስ ተፋሰሶች ላይ የአፈር መሸርሸርን በተመለከተ እየተከናወኑ ባሉ የምርምር ሥራዎች ዙሪያ በፕሮጀክቱ 2 ዙር የ3 ዲግሪ ትምህርት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች ባሉበት ጥር 5/2015 ዓ/ም ሰሚናር አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በ‹‹AMU-IUC›› ፕሮግራም የፕሮጀክት IV አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቶሮራ እንደገለጹት በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ዙር ሥራ ሦስት የ3 ዲግሪ ተማሪዎች በቤልጂየም እና ሁለት የ3 ዲግሪ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ3 ዲግሪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጎ በምርምሮቻቸውም በአካባቢዎቹ የአፈር መሸርሸር ችግርን የመለየት ሥራ እንዲያጠኑ ተደርጓል፡፡ እንደ አስተባባሪው በ2 ዙር ፕሮጀክቱ የሚያተኩረው በመጀመሪያው ዙር የተለዩ ችግሮችን በመከላከልና መፍትሄ በማምጣት ላይ ነው፡፡ በፕሮጀክቱ የሚማሩ ተማሪዎች በትምህርትና ምርምራቸውን በሚሠሩበት ጊዜ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የምርምር ውጤቶች ወደማኅበረሰቡ እንዲደርሱ በትኩረት እንደሚሠራም አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡

በፕሮጀክቱ በመጀመሪያ ዙር የ3 ዲግሪ ትምህርት ዕድል አግኝተው ከነበሩትና በዕለቱ የምርምር ሥራዎቻቸውን ካቀረቡት አማካሪዎች መካከል የውሃ ሀብትና መስኖ ምኅንድስና ፋከልቲ መምህር የሆኑት ዕጩ ዶ/ር ዓለማየሁ ካሣዬ የሸፌና ኤልጎ ንዑስ ተፋሰሶች ላይ ባደረጉት ምርምር መሠረት ከኤልጎ ወንዝ ከፍተኛ የሆነ አፈር ወደ ጫሞ ሐይቅ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በመርሃ-ግብሩ በፕሮጀክቱ 2 ዙር የ3 ዲግሪ ትምህርት ዕድል ላገኙ ተማሪዎች ከቤልጂየም የተመደቡ የምርምር አማካሪዎች የ3 ዲግሪ የምርምር ሥራዎቻቸውን አቅርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት