አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደበበ ኃይለገብርኤል የሕግ ቢሮ ጋር በመተባበር «የብሔር ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያ የተሻለ አማራጭ ነው ወይስ ስጋት?» እንዲሁም «በፖለቲካና በኢኮኖሚ የመልካም አስተዳደር ስኬትን ለማረጋገጥ የራስን ዕድል በራስ መወሰን ትክክለኛ አማራጭ ነው ወይስ አይደለም?» በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥር 14/2015 ዓ/ም የክርክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የስነ ትምህርትና ስነ ባህርይ ሳይንስ ት/ቤት ዲን እና የሕግ ት/ቤት ዲን ተወካይ መ/ር አንለይ ብርሃኑ እንደገለጹት የክርክር መድረኩ ለማኅበረሰቡና ለመንግሥት የሚጠቅም ሃሳብ የሚገኝበት ሲሆን ኢትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ሳይንሳዊና መረጃን መሠረት ያደረጉ ሃሳቦችን በመስጠት ሀገሪቷ የጀመረችውን የለውጥ ሥርዓት ለማጠናከርና ውጤታማ ለማድረግ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡

‹‹በልዩነታችን ውስጥ የበለጠ አንድ የሚያደርገንና የሚያቀራርበን ነገር አለ›› ያሉት የሕግ ባለሙያ  አቶ ደበበ  ኃይለገብርኤል በበኩላቸው ክርክሩ ጠያቂና ሃሳብን በሃሳብ ሊሞግት የሚችል ትውልድ መፍጠርን ታላሚ ያደረገ መሆኑን ጠቁመው በሃሳብ ላይ መሟገት የምናስበውን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መፍጠር መቻል ነው ብለዋል፡፡

ክርክሩ በዩኒቨርሲቲው የሕግ ት/ቤት መምህራን የተካሄደ ሲሆን የሕግ ት/ቤት ተማሪዎችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

                                                                                                                                  የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት