አቶ ግርማ ታደሰ ከአባታቸው አቶ ታደሰ መርቼ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ወለቱ ሙንዶ በ1980 ዓ/ም በባስኬቶ ልዩ ወረዳ ዶኮ አይማ ቀበሌ ተወለዱ፡፡

አቶ ግርማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ልማት ሙሉ 1 ደረጃ ትምህርት ቤት በመደበኛው እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በማታው ፕሮግራም ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

አቶ ግርማ ከግንቦት 1/1996 ዓ/ም እስከ ጥር 30/1998 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው በጉልበት ሠራተኛነት፣ ከጥቅምት 21/1999 ዓ/ም እስከ 2002 ዓ.ም በጽዳት ሠራተኛነት፣ ከሐምሌ 15/2002 ዓ/ም እስከ የካቲት 30/2005 ዓ/ም በሾፌር ረዳትነት፣ ከ2005 ዓ/ም እስከ  ሰኔ 09/2008 ዓ/ም በከባድ መኪና ሾፌር ረዳትነት፣ ከነሐሴ 10/2008 ዓ/ም እስከ ግንቦት 30/2009 ዓ/ም በጊዜያዊ ቅጥር በሾፌርነት እንዲሁም ከሰኔ 01/2009 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በቋሚ ቅጥር በሾፌር II ደረጃ በሾፌርነት አገልግለዋል፡፡ 

አቶ ግርማ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በ35 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አቶ ግርማ የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበሩ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ግርማ ታደሰ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ለሥራ ባልደረቦችና ጓደኞች እና ለዩኒቨርሲቲው መኅበረሰብ መፅናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት