Print

አቶ ሰለሞን ንጉሤ ከአባታቸው አቶ ንጉሤ ጨሬ እና ከእናታቸው ወ/ሮ እቴነሽ ተሾመ በአርባ ምንጭ ከተማ በ1979 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

አቶ ሰለሞን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን በኩልፎ መለስተኛ 2 ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2 ደረጃ ት/ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን በመቀጠልም ከግንቦት 10/2001 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 24/2002 ዓ.ም በአሌልቱ ፖሊስ ማሠልጠኛ ት/ቤት በ22 ዙር መደበኛ የፖሊስነት ሙያ ሥልጠና አጠናቀው የምስክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡

አቶ ሰለሞን ከመስከረም 01/2001 ዓ/ም እስከ መጋቢት 30/2005 ዓ/ም በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በድሬዳዋ ማረሚያ ቤት በጥበቃ አባልነት እንዲሁም ከሚያዝያ 01/2005 ዓ/ም ጀምሮ በቲም ኦፌሰርነት፣ ከ2008 ዓ/ም እስከ 2010 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጥበቃ አባልነት እና  ከ2010 ዓ.ም እስከ 2012 ዓ.ም  የጤና አጠባበቅ ጣቢያው ጥበቃ አስተባባሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከመጋቢት 1/2012 ዓ.ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኩልፎ ካምፓስ የጥበቃ አባል በመሆን ተቋሙን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ ሰለሞን ባለትዳርና የ አንዲት ሴት ልጅ አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ36 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ሰለሞን ንጉሤ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ለሥራ ባልደረቦቹና ጓደኞቹ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት