Print

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ1979 ዓ/ም ከተመሠረተ ጀምሮ አያሌ ኢትዮጵያውያንን በውሃ ምኅንድስና ዘርፍ ቀዳሚ አድርጎ ሲያሠለጥን የቆየ ሲሆን ወደ ዩኒቨርሲቲነት ካደገበት ከ1996 ዓ/ም ጀምሮ በበርካታ የምኅንድስና፣ የጤና፣ የግብርና፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነሰብ፣ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ እንዲሁም በሕግ እና በስነትምህርትና ስነባህሪ ዘርፎች ምሁራንን በማፍራት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዩኒቨርሲቲው  በስሩ 6 ኮሌጆች፣ 2 የውሃ ቴክኖሎጂ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች፣ 4 ትምህርት ቤቶች፣ 1 የስፖርት አካዳሚ፣ 7 የምርምር ማዕከላትና 1 የባህልና ቋንቋ ምርምር ኢንስቲትዩት ያቀፈ ነው፡፡ በመማር ማስተማር ዘርፍም በ75 የቅድመ-ምረቃ፣ በ140 የ2 ዲግሪ እና በ34 የ3 ዲግሪ በድምሩ በ174 የድኅረ ምረቃ በአጠቃላይ በ249 የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን በመደበኛው እና በተከታታይና ርቀት ትምህርት መርሃ-ግብሮች በዋናው ግቢ፣ ነጭ ሣር፣ ዓባያ፣ ጫሞ፣ ኩልፎ እና ሳውላ በድምሩ በ6ቱ ካምፓሶች ተማሪዎችን በማሠልጠን ላይ ይገኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም የመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛው መርሃ ግብር በ75 የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምር ይሆናል:: ለተጨማሪ መረጃዎች ድረ-ገጻችንንና ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይከታተሉ፡፡

 

https://www.amu.edu.et

https://t.me/arbaminch_university

https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

The Center of Bright Future!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት