በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ በእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነጽሑፍ ት/ክፍል በ‹‹English Language Teaching (ELT)›› ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ዕጩ ዶ/ር ጋሻው ተፈራ እና ዕጩ ዶ/ር ተፈሪ ሀቱዬ የመመረቂያ የምርምር ሥራቸውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎቻቸው በተገኙበት ጥር 24 እና 25/2015 ዓ/ም አቅርበዋል፡፡  የሁለቱም ዕጩ ዶክተሮች የመመረቂያ ጽሑፎች በአማካሪ ቦርዶቹ ተቀባይነትን አግኝተዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ጋሻው ተፈራ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲፕሎማ ከሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፣ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነጹሑፍ እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንግሊዝኛን እንደ ውጭ ቋንቋ ማስተማር /TEFL/ አግኝቷል፡፡ ዕጩ ዶ/ር ጋሻው የ3 ዲግሪውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር ሲከታተል የቆየ ሲሆን ‹‹The Effects of the Mobile-Based Aural and Oral Skill Instructions on the Aural Comprehension and Oral Skill Performances of EFL Teacher Trainees in Arba Minch Teacher Education College›› በሚል ርዕስ የመመረቂያ ጥናቱን አከናውኗል፡፡

በተመሳሳይም ዕጩ ዶ/ር ተፈሪ ሀቱዬ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲፕሎማ ከሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፣ የመጀመሪያ ዲግሪውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር ከዲላ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እና የሁለተኛ ዲግሪውን ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ  በተመሳሳይ የትምህርት መስክ አግኝቷል፡፡ ዕጩ ዶ/ር ተፈሪ የ3 ዲግሪውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር ሲከታተል የቆየ ሲሆን በ‹‹English Language Teachers’ Perception, Perceived Practice, and Predictors of Experiential Learning from Three Perspectives: Some Selected Primary School Teachers in Gamo and Gofa Zones›› በሚል ርዕስ የመመረቂያ ጥናቱን አካሂዷል፡፡

 ዕጩ ዶ/ር ጋሻው ተፈራና ዕጩ ዶ/ር ተፈሪ ሀቱዬ 3 ዲግሪያቸው በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሲያጸድቅ የሚሰጣቸው  መሆኑ ተገልጿል፡፡

 የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት