አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን ካሉ አንጋፋና ስመ ጥር ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን መልካም ስም በገበያ አማራጭነት ለመጠቀም ያሰቡ አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች የዩኒቨርሲቲው ያልሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች እና የተማሪ ውጤት ኮፒዎች ላይ የዩኒቨርሲቲውን ሎጎ ተጠቅመው የዩኒቨርሲቲውን ስም እያጎደፉ መሆኑን ከተለያዩ ተቋማት ከሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ጥያቄዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡

ስለሆነም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስም የተመዘገበ የትምህርት ማስረጃ እና የተማሪ ውጤት ኮፒ በመያዝ ሠራተኛ ቀጥራችሁ የሚታሠሩ ተቋማት የሠራተኞቻችሁን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት እንዲታረጋግጡ እና በሚረጋገጠው መረጃ መሠረት በወንጀል ተግባር የተሳተፉ ግለሰቦች በሕግ አግባቢ ተጠያቂ እንዲደረጉ አጥብቀን እናሳውቃለን፡፡

የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት የማጣሪያ አማራጮች:-

1.  የተመራቂውን የትምህርት ማስረጃ ከደብዳቤ ጋር በመያዝ በአካል ዩኒቨርሲቲ በመምጣት ወይም

2. በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ www.amu.edu.et ላይ SMIS የሚለው ቁልፍ (Button) በመንካት ከታች ባሉ Dashboard ላይ Forgery Check በሚል የተፃፈ ቦታ ላይ የተመራቂውን የመታወቂያ ቁጥር በማስገባት ተመራቂው በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስለመመረቁ እና በየትኛው መርሃ ግብር፣ በየትኛው የትምህርት ዘርፍ እንደተመረቀ ማረጋገጥ ይቻላል። ሆኖም ይህ 2ው አማራጭ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ ለተማሩት የቅድመ ምረቃ እና ከ2007 ጀምሮ ለተማሩት የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የሚሠራ ነው። ነገር ግን በ CGPA ልዩነት የተሠሩ ሐሰተኛ ማስረጃዎችን ለማጣራት አያስችልም።

3. በአካል መቅረብ የማይችሉ አጣሪ ተቋማት ለቅጥር የቀረበውን የትምህርት ማስረጃ እና የጥያቄ ደብዳቤ ጥሩ ስካን ኮፒ ለ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ወይም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. በመላክ ምላሽ ማግኘት ይቻላል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት