በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በእንስሳት ሳይንስ ት/ክፍል በእንስሳት ስነ-ምግብ ‹‹Animal Nutrition›› ትምህርት ፕሮግራም ላለፉት 6 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ጌታቸው አብርሃም የምርምር ሥራውን መጋቢት 28/2015 ዓ/ም የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የመጀመሪያ ዲግሪውን ከቀድሞው የሀዋሳ ግብርና ኮሌጅ፣ የሁለተኛ ዲግሪውን ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ  በማግኘት  በሚዛን ቴፒ ቲቪኢቲ ግብርና ኮሌጅ እና በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሲያገለግል ቆይቶ የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በ2010 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዕድሉን አግኝቶ የጀመረው ዕጩ ዶ/ር ጌታቸው የመመረቂያ ጽሑፉን በ‹‹INDIGENOUS LEGUME FODDER TREES AND SHRUBS IN GAMO ZONE, ETHIOPIA: EMPHASIS ON ECOLOGICAL VALUE, NUTRITIONAL QUALITY AND METHANE EMISSION POTENTIALS›› በሚል ርዕስ ላይ አከናውኗል፡፡

ዕጩ ዶ/ር ጌታቸው የዶክትሬት ዲግሪያቸው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኙ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎችን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች፣ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊና የዘርፉ መ/ራን ተገኝተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት