የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ሚያዝያ 30/2015 ዓ/ም ባካሄደው ጉባዔ ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን የዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝደንትና የአስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ተወካይ ሆነው ሲያገለግሉ በቆዩበት ጊዜ ያከናወኑት የሥራ አፈጻጸም በዩኒቨርሲቲው ቦርድና ሴኔት በጣም ጥሩ ሆኖ በመገምገሙ ወ/ሮ ታሪኳ በምክትል ፕሬዝደንት ኃላፊነት የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ለሁለተኛ ዙር እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡

ቦርዱ በመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራርና የአስተዳደር ኃላፊዎች ምርጫ እና ሹመት ወይም ምደባ መመሪያ ቁጥር 002/2011 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 6.5 ተራ ቁጥር 4 እና በምርምር ዩኒቨርሲቲዎች የከፍተኛ አመራር ቦታዎች አደረጃጀት መሠረት ውሳኔውን ማስተላለፉን አሳውቋል፡፡

ወ/ሮ ታሪኳ ዩኒቨርሲቲውን ከመጋቢት 07/2011 ዓ/ም ጀምሮ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት እንዲሁም ከታኅሣሥ 23/2014 ዓ/ም ጀምሮ የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ተወካይ ሆነው ደርበው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት