በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ ̋Biotechnology” ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ሳምሶን ትዕዛዙ የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ማጠናቀቂያ የምርምር ሥራውን መስከረም 4/2016 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ሳምሶን የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹Evaluating azo dye biodegradation potential of halotolerant and thermo-alkaliphilic bacteria from Shala hot spring, Ethiopia›› በሚል ርዕስ ያከናወነ ሲሆን የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

ዕጩ ዶ/ር ሳምሶን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በፋራጎሳ፣ ኩልፎና አርባ ምንጭ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማጠናቀቅ ዲፕሎማውን በባዮሎጂ ትምህርት ከሀዋሳ  የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ1995 ዓ/ም፣ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በበባዮሎጂ በ2001 ዓ/ም እና ሁለተኛ ዲግሪውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Biotechnology›› በ2006 ዓ/ም አጠናቋል፡፡ ዕጩ ዶ/ር ሳምሶን የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮቴክኖሎጂ ትምህርት ፕሮግራም ሲከታተል ቆይቷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ፕ/ር ስዩም ሌታና ዶ/ር አዲስ ስማቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በውጭ ገምጋሚነት እንዲሁም በግምገማ ዶ/ር አክበር ጩፎ በውስጥ ገምጋሚነት የተሳተፉ ሲሆን የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎችን ጨምሮ የኮሌጅ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ የዘርፉ መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ታድመዋል፡፡

ዕጩ ዶ/ር  ሳምሶን ትዕዛዙ የዶክትሬት ዲግሪው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኝ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት