መ/ር ተስፋዬ ፈረደ ገ/ማርያም ከእናታቸው ከወ/ሮ እቴነሽ ተፈራ ከአባታቸው አቶ ፈረደ ገ/ማርያም በቀድሞ ጎፋ ወረዳ ቡልቂ ከተማ ግንቦት 19/1960 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

መ/ር ተስፋዬ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቡልቂ ከተማ ፊታውራሪ አስፋው እንግዳየሁ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሳውላ 2ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል፡፡

መ/ር ተስፋዬ ፈረደ ከሀዋሳ መምህራን ትምህርት ተቋም በ/TTI/፣ ከሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በእንግሊዘኛ ቋንቋ በዲፕሎማ፣ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዝኛ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ተከታትለው ተመርቀዋል፡፡  

መ/ር ተስፋዬ ከ1978 ዓ/ም - መስከረም 30/2009 ዓ/ም በጎፋ አካባቢ በሚገኙ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በሳውላ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት በመ/ርነት፣ ከጥቅምት 1/2009 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሌክቸረር አካዳሚክ ማዕረግ  በሳውላ ካምፓስ በእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህርነት እንዲሁም በካምፓሱ የተቋማዊ ጥራት ማጎልበቻ አስተባባሪ በመሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ አገልግለዋል፡፡ 

መ/ር ተስፋዬ ባለትዳርና የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ኅዳር 4/2016 ዓ/ም በ56 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመ/ር ተስፋዬ ፈረደ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት