Print

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሒሳብ ት/ክፍል በ‹‹Numerical Analysis›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ወንድምአገኘሁ ስምዖን የካቲት 26/2016 ዓ/ም የምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ወንድምአገኘሁ ስምዖን የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ሁለተኛ ዲግሪውን ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ በሒሳብ ትምህርት አግኝቷል፡፡ ዕጩ ዶ/ር ወንድምአገኘሁ ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Numerical Analysis›› የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየ ሲሆን የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹Numerical Treatment of a Class of Singularly Perturbed Parabolic Differential Difference Equations with Integral Boundary Condition›› በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

ዶ/ር ዐወቀ አንዳርጌ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲና ዶ/ር ዘርይሁን ክንፈ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ ጽሑፉ የውጭ ገምጋሚ ሲሆኑ ዶ/ር እያያ ፈቃደ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ገምጋሚ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

የዕጩ ዶ/ር ወንድምአገኘሁ የግምገማ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴነት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት