Print

አቶ ሸለሞ ጫልታ ከአባታቸው አቶ ጫልታ ፀጋዬ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ወርቅነሽ የሶ በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር መሎ ኮዛ መስከረም 3 /1968 ዓ/ም ተወለዱ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አባያ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡

አቶ ሸለሞ  ከሐምሌ 24/1981 - ግንቦት 30/1998 ዓ/ም በቀድሞ በጋሞ ጎፋ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በአርባ ምንጭ ዓሳ አስጋሪዎች ሁለገብ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበር በዓሳ አስጋሪነት እና በጀልባ ኦፕሬተርነት፣ ከሰኔ 21/1998 ዓ/ም- ነሐሴ 25/1999 ዓ/ም በአዲስ አበባ በኢ/ካ/ፍ/ኮ/አ/ማኅበር በጊዜያዊ የጥበቃ ሠራተኛነት፣ ከታኅሣስ 28/2002 ዓ/ም- ግንቦት 30/2005 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ጸጥታና ደኅንነት ጽ/ቤት በኮንትራት ቅጥር በዩኒቨርሲቲ ፖሊስነት፣ ከሰኔ 1/2005 ዓ/ም- ጳጉሜ 5/2010 ዓ/ም በቋሚ ቅጥር በዩኒቨርሲቲ ፖሊስነት፣ ከመስከረም 01/2011 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በዋናው ግቢ የውሃ ዋና አሠልጣኝና ሕይወት አዳኝ ሠራተኛ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ ሸለሞ ጫልታ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መጋቢት 29/2016 ዓ/ም በተወለዱ በ48 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አቶ ሸለሞ ባለትዳር እና የ5 ልጆች (3 ወንድ እና 2 ሴት) አባት ነበሩ፡፡  

ዩኒቨርሲቲው በአቶ ሸለሞ ጫልታ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና ሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት