ግዙፍ የማስተማሪያ፣ የምርምር እንዲሁም የሕክምና ማዕከል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነገ ሰኔ 29/2016 ዓ/ም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ወቅቱን በዋጁ ዘመናዊ የሕክምና መስጫና የምርምራ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀውና የሄሊኮፕተር አምቡላንስ አገልግሎት ጭምር እንዲሰጥ ሆኖ የተገነባው ሆስፒታሉ ከሰባት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የአካባቢውና የአጎራባች ክልሎችና ዞኖች ነዋሪዎች በአጠቃላይና በስፔሻሊቲ ደረጃ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷል፡፡

በተያያዘም ዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ተግባራትን የሚያሳይ ኤግዚቢሽን በዋናው ግቢ አዘጋጅቶ እንግዶቹን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ኤግዚብሹኑ በነገው  ዕለት ለጎብኚዎች ክፍት መሆኑን እየገለጽን እንድትጎበኙ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት