የ2010 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

የዩኒቨርሲቲው የ2010 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የስራ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ሐምሌ 20/2010 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡
የስትራቴጂክ ዕ/ዝ/ት/ግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዝሙ ቀልቦ ባቀረቡት የማጠቃለያ ሪፖርት በትምህርት ጥራትና በመማር ማስተማር፣በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት፣ በመልካም አስተዳደርና በቢዝነስና ልማት ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝርና ያጋጠሙ ችግሮች  ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በሪፖርቱ እንደተገለፀው በ2010 በጀት ዓመት ከተከናወኑ ተግባራት መካከልየትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አንፃር የሴት ተማሪዎችን ተሳትፎና ውጤታማነት ለማረጋገጥ የማጠናከሪያ ትምህርትና ተከታታይ ምዘና መሰጠቱ፣ተማሪ ተኮር የማስተማር ዘዴ በሁሉም የትምህርት አይነቶች ተግባራዊ መደረጉ፣የመምህራንና ተማሪዎች 1 ለ 5 አደረጃጀትተጠናክሮ መቀጠሉ፣ በመደበኛና ተከታታይ አዳዲስ የቅድመ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞችመበራከታቸው፣ልዩ ድጋፍ የሚሹ120 ተማሪዎች ውጤታማ ሆነው እንዲያጠናቅቁ መደረጉ፣የትምህርት ክፍለ ጊዜ ብክነትን በመቀነስ በመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜትምህርትወቅቱን ጠብቆ መጀመሩ፣ ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ ተማሪዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የማህበራዊ ሳይንስ ምጣኔን ያሳካ መሆኑ፣ የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ በውጤት ተኮር ስርዓት ተዘጋጅቶ በየደረጃው ባሉ የስራ ዘርፎች ከከፍተኛ አመራር እስከ ፈፃሚው ድረስ የዕቅድ ውል ስምምነት መፈራረሙ፣የተደራጁና የዩኒቨርሲቲውን ገፅታ የሚያንፀባርቁ ጠቃሚ መረጃዎች በመገናኛ ብዙሃን መሰራጨታቸውእንዲሁም የIFRSና የማስተማር ክህሎት ስልጠና መሰጠቱዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በተጨማሪምየሴት መምህራንን የምርምር አቅም ለማሳደግ የምርምር ንድፈ ሃሳብ ዝግጅትናየምርምር ጽሁፍችን በታወቁ ጆርናሎች ለማሳተም የሚያስችል የአፃፃፍ ዘዴና ሶፍትዌር ስልጠና መሰጠቱ፣ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ፣ የተለያዩ የምርምር ጆርናሎች ታትመው መሰራጨታቸው፣ የምርምር አውደ ጥናቶች መካሄዳቸው፣ ነፃ የሕግ አገልግሎት መሰጠቱና በዩኒቨርሲቲው አካባቢ በሚገኙ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ 70 የመንግሥት ሠራተኞች ነፃ የትምህርት እድልእንዲያገኙ መደረጉ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ከተገኙ ስኬቶች መካከል ናቸው፡፡
የአስተዳደር እና የቢዝነስና ልማት ዘርፍን አስመልክቶየአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታየማመቻቸትና ተግባራዊነቱን የመከታተል ስራ መሰራቱ፣ የማማከር አገልግሎት ለተማሪዎች በተፈለገ ጊዜና ጥራት መሰጠቱ፣ የፋይናንስና በጀት አስተዳደር ህጎች፣ደንቦች፣ መመሪዎችና ተጨማሪ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓቶች ተዘርግተው ተግባራዊ መደረጋቸው፣ክፍትየሥራ መደቦችን በሠራተኞች ከማሟላት አንጻር 495የአስተዳደር ድጋፍ ሰጪሰራተኞች እና 356መምህራንቅጥር መካሄዱ እና169 መ/ራንና189የአስተዳደር ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የደረጃ ዕድገት ማግኘታቸው፣ የአባያ የጫሞና የነጭ ሳር ካምፓሶች Solid west ከGray Waterየመለየት ሥራበጫሞና በሳውላ ካምፓስ የተማሪዎች ማደሪያ ግንባታ መጠናቀቁ፣በዋናው ግቢ ከማስፋፊያ ግንባታዎች ውስጥ በዮቴክ ኮንስትራክሽን የተገነቡ ግንባታዎችን የመጨረሻ ርክክብ ተደርጎ የሰነድ ዝግጅቶች መከናወናቸው፣በጫሞና በአባያ ካምፓስ የተገነቡ የተለያዩ ህንፃዎችን ጊዜያዊና የመጨረሻ ርክክብ ለማድረግ ቅድመ ርክክብ ዳሰሳ ተደርጎ የእርምት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መገኘታቸውና የግንባታ ስራዎች ክትትል በቋሚነት መካሄዱ እንዲሁም  የህፃናት ማቆያ መቋቋሙከተመዘገቡ ስኬቶች መካካል ተጠቅሰዋል፡፡

በአንፃሩ የመ/ራን ፍልሰት፣ የእርሻ መሬቶች በበቂ ሁኔታ አገልግሎት ላይ አለመዋላቸው፣ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ አለመቋቋም፣ በሳውላ ካምፓስ የኢንተርኔት፣ የላቦራቶሪና ክሊኒክ እጥረት መኖሩ፣ ያልተማከለ አሰራር መኖሩ፣ የJEG ምደባ መዘግየት፣ የግንባታዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ አለማለቅ፣ በአመራርነት ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ ማነስ፣ የተሽከርካሪ እጥረት፣ የመብራት መቆራረጥ፣ የማዕቀፍ ግዢዎች መዘግየትና የግዢ ስርዓት መጓተት፣ በአንዳንድ የስራ መደቦች የባለሙያ ዕጥረት እንዲሁም የግንባታ ጥሬ ዕቃ መናር የመሳሰሉት በአፈጻፀም ወቅት የታዩ  ችግሮች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የአፈፃፀም ክፍተት ያለባቸውንና ያልተከናወኑ ተግባራትን ለይቶ በቀጣይ በማቀድ መስራት እንደሚገባና የትምህርት ጥራትና የመልካም አስተዳደር ፎረም ውይይቶችን እንደ ግብዓት በመውሰድ ከተማሪዎች፣ ከመምህራንና ከአስተዳደር ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ጋር የተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማስተካከልና አጠናክሮ ለመስራት ማቀድ ይገባል ብለዋል፡፡
በሪፖርት ግምገማው የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝደንት ጨምሮ ም/ ፕሬዝደንቶች፣ የየኮሌጁ ዲኖችና ዳይሬክተሮች እንዲሁም የየስራ ክፍል ተጠሪዎችና ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡ ሪፖርቱን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ ጥያቄዎችና ግምገማዊ አስተያየቶች ተነስተው በሚመለከታቸው ክፍሎች ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን በሪፖርቱ ያልተካተቱ ነጥቦች እንዲካተቱም ከቤቱ ጥቆማ ተደርጎበታል፡፡