ዩኒቨርሲቲው STEMpower ከተሰኘ ዓለም ዓቀፍ መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት Arba Minch STEMpower Center የተባለ ማዕከል በአርባ ምንጭ ለማቋቋምና ለማጠናከር የካቲት 13/2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ምስሎቹን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

በውል ስምምነት ፊርማ ሰነዱ ላይ እንደተብራራው የውል ስምምነቱ ዋና ዓላማ ማዕከሉ የሂሳብና ሣይንስ ትምህርት የማጠናከር እንዲሁም የሣይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የምህንድስናና የሂሳብ መለማመጃ ማዕከላትን የማስተዋወቅና የማጎልበት ተግባራት ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመተባበር የማከናወን፣ ዓመታዊ ዕቅድ መከታተል፣ መገምገምና የማጽደቅ ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡

የተለያዩ የቴክኒክና አስተዳደራዊ ስልጠናዎችንና ድጋፎችን Online እና በአካል መስጠት፣ የሠራተኞች ደመወዝና የደረጃ ዕድገት መሥራት፣ የማዕከሉን ሥራ ማስተዋወቅና የፋይናንስ ጉዳዮችን ማስተዳደር፣ የፋይናንስ ዕቅዶችን መወሰን፣ ወጪንና ክፍያዎችን ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመመካከር ተግባራዊ ማድረግ በSTEMpower የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡

የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ ከአርባ ምንጭ STEMpower ማዕከል ጋር በጋራ መሥራት፣ የማዕከሉን ተልዕኮና እሴት ሊያጎለብቱ የሚችሉ የአጋርነት ስምምነቶችን መፈራረም እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመተባበር የማዕከሉን አስተባባሪ የአገር ውስጥ ባለሙያ መቅጠር የSTEMpower ተጨማሪ ሥራዎች ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ኃላፊነትና ተግባራት ደግሞ የአርባ ምንጭ STEMpower ማዕከል ሥራዎችን መከታተል፣ መገምገም፣ ማስተዳደር፣ ሥርዓተ-ትምህርት መቅረጽ፣ የማዕከሉን የትምህርት ሥራ መደገፍ፣ ወጣቶች ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት መሥራት፣ ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት፣ የሴቶችና ልጃገረዶች ትምህርትና እኩልነትን ለማጎልበት አዳዲስ ሀሳቦችንና ግኝቶችን መፍጠርና መደገፍ፣ በአገር አቀፍ የሣይንስ ቀንና ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ላይ መሳተፍ እንዲሁም በኢትዮጵያና በአፍሪካ በሚዘጋጁ የሣይንስና ፈጠራ ስራዎች ውድድሮች ላይ መሳተፍ፣ የማዕከሉን የአፈፃፀም ሪፖርት መገምገምና የማዕከሉን ሥራ በተለያዩ ሚዲያዎች ማስተዋወቅ እንደሆነ በሰነዱ ላይ ተመላክቷል፡፡

STEMpower የተሰኘው መቀመጫውን U.S.A. ያደረገ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግና ሂሳብ ትምህርቶች በአገራችን 13 ማዕከላትን ከፍቶ ዩኒቨርሲቲዎችን እየደገፈ ይገኛል፡፡