የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ጋር በመተባበር ‹‹ጠንካራ እና ታማኝ ሐኪም ለተሻለ ጤና!›› በሚል መሪ ቃል በኮሌጁ ሥር ለሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ታኅሣሥ 17/2013 ዓ/ም በሙያ ማሻሻያ ዙሪያ ሥልጠና የሰጠ ሲሆን የጋራ መግባቢያ ሰነድም ተፈራርሟል፡፡   ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከIBRO እና DANA ፋውንዴሽኖች ጋር በመተባበር የአንጎል ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ለኮሌጁ መምህራን፣ ተመራማሪዎችና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም ለመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከታኅሣሥ 12-16/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በጎ አድራጎት ክበብ አባላት ከጥቅምት 22 እና 23/2011 ዓ/ም  ጫማ የመጥረግ ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል፡፡